ዮክሬን በሩሲያ መዲና ላይ ግዙፉ የድሮን ጥቃት ፈጸመች
AI Summary
Ukraine conducted a significant drone attack on a Russian city, marking one of the largest such assaults since the conflict began. Reports indicate multiple casualties and numerous drone intercepts by Russian air defenses.
ዩክሬን ለሁለት ተከታታይ ምሽቶች ምስኮ ላይ የድሮን ጥቃት አደረሰች ። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት ወደ 926 የሚጠጉ የዩክሬን ድሮኖችን ማምከን ተችሏል፤ ይህም ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ዩክሬን ካደረሰቻቸው ጥቃቶች ሁሉ ግዙፉ እንደሆነ ተነግሮለታል። የሞስኮ ከንቲባ ሰርጌ ሶብያን እንዳሉት፣ ከእሁድ ምሽት ጀምሮ 350 የዩክሬን ድሮኖች ወደ ከተማዋ ተተኩሰዎል፤ አብዛኞቹ ግን በአየር መከላከያ ተመትተው ሰማይ ላይ ሳይደርሱ ወድመዋል። የሞስኮ ክልል አስተዳዳሪ አንድሬይ ቮሮብዮቭ እንዳሉት፣ በጥቃቱ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች አምስት ቆስለዋል። The post ዮክሬን በሩሲያ መዲና ላይ ግዙፉ የድሮን ጥቃት ፈጸመች appeared first on Ethiopia Observer.